ኮሚሽኑ ሳምንታዊ የሌማት ትሩፋት የሥራ ዕንቅስቃ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ኮሚሽኑ ሳምንታዊ የሌማት ትሩፋት የሥራ ዕንቅስቃሴን ገምግሟል።

ኮሚሽኑ ሳምንታዊ የሌማት ትሩፋት የሥራ ዕንቅስቃሴን ገምግሟል።


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም



የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን በሳምንቱ ውስጥ ያለውን የሌማት ትሩፋት የሥራ እንቅስቃሴና መደበኛ ሥራዎች ከክፍለ ከተማ የዘርፉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በሆን ገምግሟል።
የአርሶ አደር ማቋቋም እና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ነባር ተጠቃሚዎችን ከማስቀጠል፣ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ወደ ዘርፉ ከማስገባት፣ የሥራ ዕድል ከመፍጠርና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ሥራዎች መሰራቱን አንስተዋል።
አያይዘውም ከተማ ግብርና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያ ድርሻው ከፍተኛ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ኢኮኖሚያዊ ድርሻ በተሳካ ሁኔታ ማሳካት እንዲቻል በቴክኖሎጂና በግብዓት በበቂ ሁኔታ መደገፍ ይገባል ብለዋል።
የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ሊጋኔ የከተማ ግብርና በከተማ አስተዳደሩ ልዮ ትኩረት ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል አንድ መሆኑን እና ኢኮኖሚያዊ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም ዕቅድን መሰረት ያደረገ ከስፔሻሊስት በዘለለ ጀነራሊስት በሆነ መንገድ ውጤት ማምጣት የሚያስችል ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል። ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍና ክትትል በአግባቡ የተገልጋዮን ፍላጎት መሰረት ባደረገ አግባብ መደረግ ያለበት መሆኑንም ተናግረዋል።
ከመረጃ አያያስና ከሪፖርት ጋር በተያያዘም የተናበበና ጥራት ያለው መረጃ ማደራጀትና ተናባቢ በሆነ አግባብ ወቅቱን ጠብቆ መላክ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድን መሪዎች እና የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በየጊዜው ግምገማ እየተደረገ ግብረ መልስ እየተሰጠ መሄዱ መልካም መሆኑን ገልፀዋል። ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑንም አንስተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments