
ከሸማችነት ወደ አምራችነት!።
ከሸማችነት ወደ አምራችነት!።
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው ኤግዚብሽንና ባዛር እንዲሁም በሁሉም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸው ተገለፀ ።
የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሺን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዪ ሽጉጤ፣ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻን ጨምሮ የክፍለ ከተማው የኑሮ ውድነትና የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል አባላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በባዛሮቹና በሁሉም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ምርቶች በአንድ ማዕከልና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸውን ተመልክተዋል።
ለበዓል የሚሆን እንቁላል፣ በግ፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ አይብ ጨምሮ ሌሎች የግብርና ምርቶች አርሶአደሮች እና አምራቾች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸውን ተመልክቷል ።
የክፍለ ከተማው የኑሮ ውድነትና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል ነዋሪው ከአምራቹ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪውን አቅርቧል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments