በእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት ከ52 ሚሊ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

በእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ የሀገር ውስጥ ትስስር መፍጠር ተችሏል።

በእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ የሀገር ውስጥ ትስስር መፍጠር ተችሏል።


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም


የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት በማቋቋም ከከተማው እድገት ጋር አብረው እንዲለሙ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር የግብርና ምርት የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት በማዕከሉ ውስጥ የሚመረቱ ጥራት ያላቸው እንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በዝቅተኛ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረበ ይገኛል።


በማዕከሉ የሥራ አመራር እና ገበያ ልማት ቡድን መሪ ወ/ሮ ሣራ ንጉሤ ባለፉት 11 ወራት 373.3 ቶን የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት ለገበያ በማቅረብ ወደ 52,143,434.00 ብር የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር መፍጠር የተቻለ ሲሆን ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ ምርት እሴት ሰንሰለቱን ጠብቆ  ለህብረተሰቡ ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል። 


አክለውም በማእከሉ የሚገኙ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የአደረጃጀት ሪፎርም ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚያዚያ ወር ክምችትን ጨምሮ በግንቦት ወር ወደ 496,000 የሚጠጋ የእንቁላል ምርት በአቧሬ ሴቶች አደባባይ፤ በማእከሉ ባሉ ሱቆች በኩል እንዲሁም ለመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በትስስር ማሰራጨት የተቻለ መሆኑን አንስተዋል። 


በቅርቡም ተቋሙ በቂርቆስ ክ/ከተማ ተጨማሪ ሱቆችን በመክፈት የእንቁላል ዋጋ መናርን ለማረጋጋት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ መሆኑንና ተጠቃሚዎችም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።


የመረጃ ምንጫችን፡- የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments