
ተቋሙ የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት ሥራ ምዘና አካሄደ፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የከተማ ግብርና ሥራዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በትኩረት እየተሰራባቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣ ሰፋፊ የከተማ ግብርና ኢንቨስትመንት አማራጮችንና እምቅ አቅሞችን መለየትና መጠቀም፣ የከተማ ግብርና ሥራዎች የሚስፋፉበትን እና የሚጠናከሩበትን ስልት መቀየስ እንዲሁም በዘርፉ ለተሰማሩ ተጠቃሚዎች የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት፣ ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ የኮሚሽኑ ዋንኞቹ ተግባራት ናቸው፡፡
በመሆኑም ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ምዘና አቶ ዘውዴ ተፈራ ከከንቲቫ ጽ/ቤት፣ አቶ ክንፈ ፍቅሬ ከፐፕሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ እና አቶ መሀመድ ካሳከፕላን ኮሚሽን ምዘናውን አካሂደው ማጠቃለያ ተሰጥቶበት ተጠናቋል ፡፡
ኮሚሽኑ ከቅንጅታዊ አሰራር ጋር ተያይዞ መድረኮችን በተከታታይነት በማመቻቸት ሥራዎችን ከመገምገምና ከመረጃ አያያዝ ጋር በተያያዘ የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በቀጣይ ማረም እንደሚገባውም ከምዘናው ትምህርት ተወስዷል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments