
የክፍለ ከተማው አስተዳደር አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመብት ፈጠራ አገልግሎት መጀመሩን ገለፀ።
አዲስ አበባ።፤ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው አስተዳደር የሚገኙ አርሶ አደሮች እና የአርሶ አደር ልጆች ከእጅ ንኪኪ ነፃ የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኦን ላይን ሲስተም ምዝገባና የመብት ፈጠራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ እንደገለፁት የአርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች የመብት ፈጠራ ስራዎች ባለፉት አመታት አርሶ አደሩ ከይዞታው ሲገፋ መቆየቱን አስታውሰው የለውጡ መንግስት የአርሶ አደሩ ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመመለስ፣ የካሳና የምትክ ቦታ እንዲያገኙ ፣ የይዞታ ባለቤት ሆነው ማልማት እንዲችሉ የሚያስችሉ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በዛሬው እለት በክ/ከተማው በይፋ የተጀመረው በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመብት ፈጠራ አገልግሎት ሊጠናከር እና ሊሰፋ የሚገባው ነው ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ኮልፌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የአርሶ አደሩ የመብት ፈጠራ ስራዎች ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሚያረጋግጥ መልኩ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራዎች ለመስራት እንዲያስችል በዛሬው እለት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመብት ፈጠራ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቀዋል።
የመሬት ልማትና አስተዳደር ኮልፌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት በቀለ እንደተናገሩት የአርሶ አደሩ እና የአርሶ አደር ልጆች የኦን ላይን ሲስተም ተመዝግበው የመብት ፈጠራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ላልተፈለገ ወጪ እንዳይዳረጉ ከማስቀረት በተጨማሪ አርሶ አደሩ በቀጥታ የመብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
ሀላፊዋ አክለውም ከለውጡ ወዲህ የአርሶ አደሩ መብት ለማስከበር በትኩረት መሰራቱን ገልፀው በዛሬው እለትም ልኬት ተወስዶ ማህደር የተደራጀላቸው አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂ ምዝገባ መጀመሩን ገልጸዋል።
የክፍለ ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰብለ ፉርጋሳ በበኩላቸው የኦን ላይን ምዝገባው በአርሶ አደሩ ሲነሱ የቆዩ ጥያቄዎችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚመልስ በመሆኑ አርሶ አደሩ በሚፈጠርለት መብት ተወዳዳሪ የሚያደርገውን ሀብት በመፍጠር ራሱን በኢኮኖሚው ማበልፀግ ይገበዋል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments