ጤናማ ምግብ ማምረት ጤናማ ህብረተሰብ መፍጠር ነ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ጤናማ ምግብ ማምረት ጤናማ ህብረተሰብ መፍጠር ነው።

****
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1 ቀን /2017 ዓ.ም 

የከተማ ግብርናን ከማሳደግ አንፃር  ለተከታታይ 3ዓመታት አየተተገበረ ያለው የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ  ትልቁን ሚና ተጪውቷል   ያሉት  የኳራንቲን ሰርተፍኬሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮ ፀጋ ለማ(ዶ/ር)ናቸው።አያይዘውም   ጠቅላይ ሚንስትሩ የነደፊትን መርሀግብር  እንደኮሚሽን ተቀብለን በሁሉም ክፍለከተሞችና ወረዳወች   ግብዓት ከማመቻቸት  ጀምሮ  አጠቃላይ ሂደቱን  ከመቆጣጠርና ከመከታተል አንፃር ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። 

ስለሆነም  አንዱ የመንግስት  የትኩረት  አቅጣጫ  ለዜጎች የስራ እድል  መፍጠር ከመሆኑ የተነሳ   ግብርና ከማ ላይ አይቻልም የሚለውን አመለካከት ቀይሮ  አሁን ላይ  የማይቀለበስበት   ደረጃ ላይ ደርሷል  ብለዋል።

የእንስሳት ልማት  ልህቀት ማእከሉ   የልማት ተነሽ  አርሶ አሮችን  መልሶ ከማቋቋም አንፃርና  ከክልሎች ያልናነሰ ምርት ከማቅረብ አንፃር  አጠቃላይ የኮሚሽኑን  ስራ የወከለ ነው  ብሎ መውሰድ  ይቻላል  ብለዋል። 

አቶ  ሽመልስ በቂርቆስ ክ/ከ አቢወት ቅርስ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ  በጓሮ አትክልት  የተደራጁ  ማህበራት ሰብሳቢ ሲሆኑ  ወደመሀበሩ  ከተቀላቀሉ በኋላ  ደስተኛ ሆነው ኑሮአቸው እየመሩበት እንደሆነ ይናገራሉ ።ሌላኛዋ የማህበሩ አባል  ወ/ሮ  ሙንትሀ   ከዚህ በፊት ስራ እንዳልነበራትና  አሁን ላይ  ለሬሴም ሆነ ለህ/ሰቡ ንፁህና ትኩስ  ምርት በማቅረቤ ደስተኛ ነኝ  ይላሉ ።አክለውም  በኔ ህይወት ላይ ለውጥ ስላመጣልኝ  ሌሎች  ወተው እንዲሞክሩት   እመክራለሁ ይላሉ። 

መ/ር  መገርሳ ጉራራ  በግቢው የከተማ ግብርናውን አስተባባሪ ሲሆኑ   ከመማር ማስተማሩ ጎንለጎን   ከተማ  ላይ ባለው ቦታ ተጠቅሞ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተምረንበታል ብለዋል።

አቶ ሀብታሙ   በወትት ልማት ዘርፍ የተሰማሩ  ሲሆኑ  የጠቅላይ ሚንስትሩን   የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ጥሪ ተቀብለን ወደ ስራ ገብተናል  ይላሉ።ስለሆም  ለነዋሪው   በትራንስፓርት  ከቦታቦታ የልተዘዋወረና ፀሀይ ያልተመታ  ንፁህ ወተት ለነዋሪው እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል። 

ኢንጅነር  ፍስሀ ለማ ይባላሉ  በቂርቆስ  ክ/ከ  በወተት  ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ  በዘርፉ ለመሰማራት  መነሻቸው ቤተሰቦቻቸው እንደሆኑ ይናገራሉ።ይሁን እንጅ ይላሉ ወደ 40 ከሚደርሱ  ላሞች በቀን ከ 200ሊትር በላይ ወተት እናከፋፍላለን  ብለዋል። 

ገበያን  ከማረጋጋትና የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ   ጥሩ  ቢሆንም  አሁን ካለበት   ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየሰራሁ ነው ካሉ በኋላ   የመኖ  አቅርቦትን የገበያ ትስስር  እንዲፈጠርልን  የመንግስት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በቦሌ ክ/ከ  405ሄክታስ ላይ ያረፈው   የእነ ዶክተር ረጋሳ  የተቀናጀ ግብርና  ከ27እስከ 28 የሚደርስ የአትክልትና ፍራፍሬ አይነቶች እንደሚገኝ የማዕከሉ ስራአስኪያጅ  አቶ በሀይሉ ይናገራሉ።አያይዘውም  21ቋሚ እና 20 አካባቢ የሚደርሱ ጊዜያዊ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ይናገራሉ።አያይዘውም ሀገራዊ ተልዕኳችን ለመወጣት  በስራ እድል ፈጠራና ገበያን ከማረጋጋት አንፃር ሰፊ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።እንደሳቸው ገለፃ  በጓሮ አትክልቱም በርባታውም  ዓለም አቀፍ  ተወዳዳሪ   እንደሚሆኑ ገልፀውልናል። 

የቂርቆስ ክ/ከ ግብርና ጽ/ቤት  ሀላፊ  ወ/ሮ  በለጠች ተሰማ  ጤናማ  ምግብ ማምረት ጤናማ ህ/ሰብ መፍጠርነው በሚል መርህ  ለ1004 የሚሆኑ ሴቶችና ወጣቶች  በከተማ ግብርና ዘርፍ የስራ እድል ፈጥረናል  ይላሉ።በዋናነት  የኛ ስራ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ስለሆነ  እንቋላል ቅንጦት ሳይሆን በየቀኑ ልንመገበው የሚገባ ምግብ ነው  የሚለውን ሀሳብ እውን ማድረግ ነው  ይላሉ ኃላፊዋ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments