
ስራችን የግብርናውን ቤተሰብ መወከል አለበት(ዋና ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ)።
አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 2ቀን /2017 ዓ.ም
የአዲስ አባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር ሪፓርት ከጠቅላላ አመራርና ባለሙያዎች ጋር በገመገመበት ወቅት ስራችን የግብርናውን ቤተሰብ መወከል አለበት ያሉት ዋና ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ ናቸው።አያይዘውም የሰራናቸው በርካታ ስራዎች እንዳሉ ሆኖ ለታዩት አንዳንድ ክፍተቶች ምክንያት የሆነው የክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ስርዓታችን የተናጠል ጉዞ ስለነበር በቀጣይ መስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል።
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮ አቶ መለስ አሸቦ የተሰጠንን ራዕይ ተከትለን ከሄድን የአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ከተማ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት የማናሳካበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል።አያይዘውም ግብርና አንዱ እንደሀገር ምግብን ከደጁ ማግኘት በመሆኑ ዛሬ ላይ የሚነሱ ችግሮች ለነገ መፍትሄ ማምጣት መንገድ ይከፍታሉ ብለዋል።
የአርሶ ከደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮ ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ባለሙያዎቹ ስራን በኔነት ስሜት መገምገም በመቻላቸው ደስታ ተስምቶኛል ይላሉ።በተጨማሪም በ9 ወራቶች ውስጥ የመጡ ጥንካሬወችም ሆነ ድክመቶች የጋራ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።
የኳራንቲን ሰርተፍኬሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ ኮ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ስራዎቻችን ውስጣዊ ቅንጅትን መሰረት የደረገ መሆን አለበት ካሉ በኋላ በአሰራር ሂደት ካላለፍን ለውሸት ሪፓር መንጠድ ይከፍታል ብለዋል።በተጨመሪም ወርቃማ ሰኞ ላይ የሚቀርቡት ከማነቃቃት ባለፈ ትምህርታዊ ይዘቶች ያሏቸው ሰነዶች ተጠናክረው ቢቀጥሉ ብለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ሪፓርቱ የቀረበበት መንገድ ጥሩ እንደሆነ ገልፀው የትራንስፓርት ፣የግብአት፣የባለሙያ እና መድሀኒት አቅርቦት የመሳሰሉትን እንዲስተካከሉ ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም ዋና ኮ/ሩ ቀይ መስመር ወደ አረንጓዴ የሚቀየረው በስራ እንጅ በወረቀት አይደለም ካሉ በኋላ የልህቀት ማዕከሉን የርባታ ማዕከል ብቻ ሳይሆን የአግሪ ካልቸር ቱሪዝ መዳረሻ ለማድረግ እንሰራለን ብለው የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠው ውይይቱ ተጠናቋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments