
የከተማ ግብርና ልማት ውጤታማነትን ለመለካት በስታንዳርድ መተግበር ግድ ነው።
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 04 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከማዕከል እስከ ወረዳ ካለው የዘርፉ አመራር፣ ከማዕከል ዳይሬክቶሬቶች፣ ከማዕከልና ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ጋር በመሆን የ9 ወራት ሥራ አፈፃፀምን፣ የሱፐርቪዥን ሪፖርት እና የእንስሳት መኖ አቅርቦት ዳሰሳ ጥናት ላይ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከቀረቡት ሰነዶች አንፃር የመወያያ አጀንዳ የሚሆኑ ዋና ዋና ሃሳቦችን ለመነሻነት ሰጥተዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቀረቡት ሰነዶች ላይ በአስተያየትና በጥያቄ መነሳት ያለባቸውን ጉዳዮች እያነሱ ይገኛል።
የግብርና ሥራን በስታንዳርድ መምራት እና የአርሶ አደሩን የዘመናት ጥያቄ መልስ መስጠት የአመራሩ ቁልፍ ሥራ መሆኑ እየተነሳ ይገኛል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments