
ግብርና በግብዓትና በምርት ዕድገት መዘመን ማለት ነው።
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 05 ቀን 2017 ዓ.ም
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በመደበኛ ሥራዎቻችን፣ በሌማት ትሩፋት ንቅናቄ፣ በአጠቃላይ መረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀትና ትንተና፣ ከውሸት የራቀ ሪፖርት ከመላክ አንፃር፣ ሥራን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በወቅቱ ገምግሞ ክፍተቶችን ከማረም አኳያ፣ የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ወቅታዊ ግብረ-መልስ እየሰጡ ከመሄድ አንፃር ራሳችንን በሚገባ ማየት አለብን ብለዋል።
አክለውም ግብርና በግብዓት አቅርቦት እና በምርት ዕድገት መዘመን በመሆኑ ከዘመኑ ጋር መዘመን እንደማገባ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የአርሶ አደሮችን መብት ፈጠራ በተመለከተ የተሰራው ስራ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ቀሪ ስራዎችን ከሌብነትና ከብልሹ አሰራር በፀዳ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ግድ ነው ብለዋል።
አያይዘውም የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እልህ አስጨራሽ ትግል ስለሚፈልግ ሁሉም አመራር በየደረጃው በስትራቴጂ መታገል እንደሚገባ አንስተዋል።
አቶ መለስ አንሸቦ ከተማ ግብርናውን ለማዘመን የተጠቃሚዎችን መረጃ በተሟላና በጥራት መንገድ መያዝ የሁሉም አመራርና ባለሙያ ኃላፊነት መሆኑን አንስተዋል።
ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ሬጉላቶሪው ዘርፍ ላይ የተሰራው ሥራ መልካም ቢሆንም አቅምን አሟጦ ከመስራት አንፃር በተለይ ነባር ብቃት ማደስን በተመለከተ ክፍተቶች መታረም ያለባቸ መሆኑን ተናግረዋል።
የአስተዳደር ዘርፉ፣ የተጠሪ ተቋማት፣ የክፍለከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች የ9 ወራት ሥራ አፈፃፀማችን ጥሩ ቢሆንም ያለን ቀሪ ጊዜ አጭር በመሆኑ አቅምን አሟጦ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አያይዘውም ከጥቅማ ጥቅም እና ከአደረጃጀት ጋር ያሉ የሰራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥባቸው አንስተዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በቀሪ ወራት ክፍተቶቻችንን ልቅም አድርገን ከሰራተኞች ጋር የጋራ በማድረግ ቃለጉባኤ ይዞ ባለቤት መስጠትና አፈፃፀሙን መከታተል ከሁሉም አመራር እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
አክለውም የመረጃ አያያዝ ሥርዓታችንን በማዘመን ከውሸት ሪፖርት መውጣት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል (በተለይም መብት ፈጠራ ላይ) እንደሚገባ ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments