
ኦዲቲንግ ለሥራ ጥራትና ቅልጥፍና ማሳለጫ መንገድ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
ኦዲት ተጠያቂነትን ከማምጣት ባሻገር ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመታገልና በዘላቂነት ለማስተካከል አንዱና ዋነኛው የማስተማሪያ መንገድነው፡፡
ኦዲት በውስጥና በውጭ ኦዲተር አማካኝነት የሚተገበር ሲሆን የውስት ኦዲት ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸው ዘርፎች (ክፍሎች) ፋይናንስ፣ የመንግስት ግዥ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት እና የሰው ኃይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ናቸው፡፡
በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወር ሥራ አፈጻጸም 6 የኦዲት ምርመራ (4 ፋይናንሽያል ኦዲት፣ አንድ ልዩ ኦዲት (ጥቆማና የትእዛዝ ማጭበርበር ኦዲት) እና አንድ የፈሰስ ኦዲት) በተጨማሪም 2 ጊዜ ድጋፍና ክትትል ተደርጎ ከእቅድ በላይ መከናወኑን የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አረጋ ፉፋ ገልፀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ የአሰራር ክፍተቶች፣ የሰነድ ማጭበርበር (ያለአግባብ ክፍያ)፣ ደጋፊ ሰነዶችን ከወጭ ሰነዶች ጋር ያለማያያዝ፣ የውስጥ ቁጥጥር ሥር-ዓትን በየዕለቱ ለይተው የማስተካከያ እርምት እርምጃ ያለመውሰድ፣ መነሻ ሰነዶች ቅደም ተከተል ያለመጠበቅ በኦዲት የተገኙ ግኝቶች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል በልዩ ኦዲት የለሚ እንጀራ ማእከል ሥራ አፈፃፀምን ምርመራ በማድረግ የማጭበርበር ችግሮች የተገኙበትና ለተፈጠረው ችግር በኦዲት ግኝቱ መሰረት ሌብነትና ብልሹ አሰራር ፈጥረው የነበሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ሪፖርቱን አቅርበናል ብለዋል፡፡
አቶ አረጋ ፉፋ እንደገለፁት የኮሚሽኑ አመራሮች የኦዲት ግኝቶችን ለማስተካከልና የእርምት እርምጃ እየወሰዱ ለመሄድ ለሥራ ክፍሉ የተሻለ ትኩረት ከመስጠት ጀምሮ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ሥራ ክፍሉም በኦዲት የተገኙ ግኝቶች የታረሙ ስለመሆኑ በተሰጠው ግብረ-መልስ መሰረት ክትትል ያደርጋል ብለዋል፡፡
አክለውም የኦዲት ግኝቶችን በመውጫ ደብዳቤ ውይይት ከተደረገበት ጊዜና ሪፖርቱ ወጪ ሆኖ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስተካከያ ግብረ-መልስ እንደደረሳቸው በአካል ተገኝተው በእያንዳንዱ ግኝት ላይ ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት በዋና ኦዲተር መ/ቤት ምርመራ ተደርጎ እርምት እርምጃ ሳይወሰድባቸው የቆዩ ግኝቶችን በተጠየቀው ጥያቄ መሰረት አስፈላጊውን ማስተካከያ የተደረገበት ግብረ-መልስ በማዘጋጀት መረጃና ሰነዶችን አያይዘን የማሳወቅ ሥራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ኦዲት ለተቋሙ ወሳኝና ክፍተቶች ሲፈጠሩ እየተከታተለ የማሻሻያ አስተያየቶች የሚሰጥ በመሆኑ በሰው ኃይል ቢታገዝ ከዚህ የበለጠ መስራት የሚቻል መሆኑን አቶ አረጋ አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments