የትኛውን ሰንጋ ይፈልጋሉ?

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የትኛውን ሰንጋ ይፈልጋሉ?

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም


በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ለመጪው የትንሣዔ በዓል ጥራት ያላቸው የደለቡ የዳልጋ ከብቶችን ለሽያጭ አዘጋጅቷል። 


በማዕከሉ ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ የዳልጋ ከብት በማድለብ ለገበያ ማቅረብ ሲሆን ለመጭው የትንሣዔ በዓል በርካታ ሰንጋዎችን አዘጋጅቶ እንግዶቹን ይጠብቃል፡፡


የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው የልማት ተነሺ አርሶ አደር ማህበራት ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ተከታታይ ዙሮች ለገበያ የሚያቀርቡት ሲሆን ልምድና ተሞክሯቸውን ተጠቅመው የአሁኑ ከባለፉት ጊዜያት በበለጠ አድልበው አቅርበዋል፡፡ 


ማህበራቱ በባለሙያ ክትትል እና ድጋፍ በጥራት የደለቡ የዳልጋ ከብቶችን ለመጪው የትንሣዔ በዓል ያዘጋጁ በመሆኑ ይምጡ የፈለጉትን ሸምተው ይመለሳሉ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments