መደጋገፍ ኢትዮጲያዊያን ድንቅ ባህላችን ነው፡፡

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

መደጋገፍ ኢትዮጲያዊያን ድንቅ ባህላችን ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በተቋሙ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ 102 ባለሙያዎችና ሰራተኞች መጭውን የትንሣኤ በዓል ታሳቢ በማድረግ ማዕድ የማጋራት ሥራ አካሂዷል፡፡

የኮሚሽኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ ኮሚሽኑ መጭውን የትንሣኤ በዓል ታሳቢ በማድረግ ለበዓሉ የሚሆን ለ102 የኮሚሽኑ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የዶሮ እና የእንቁላል ስጦታ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ኮሚሽኑ ይህንን የማዕድ ማጋራት ማድረጉ አብሮ የመኖር ባህላችን መገለጫ ስለሆነ እኛም ከተቸገሩት ጋር አብረን በዓልን በመዋል ከጎናችሁ አለን ማለት ይገባል ብለዋል፡፡ አያይዘውም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

መረዳዳት፣ መተሳሰብ፣ መደጋገፍ፣ መልካም ምኞትን ማስተላለፍ፣ አለሁህ/ሽ መባባል የእኛ የኢትዮጲያዊያን ባህላችን በመሆኑ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከወዲሁ አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ በማለት የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ላማ (ዶ/ር) መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በማዕድ ማጋራቱ ተሳታፊ የሆኑ ሰራተኞችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments