
መረዳዳት ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው።
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል መጪውን የትንሣዔ በዓል ምክንያት በማድረግ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለተለዩ 45 አቅመ ደካሞችና ወላጅ አልባ ህፃናት ብር 150,000 የሚገመት የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሂዷል።
የአርሶ አደር ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ብርቱካን በቀለ ድጋፉ ከዚህ በላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና ወደፊት ከዚህ በተሻለ ሁኔታ እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል::
የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ማዕከሉ ከሚሰራው ዋና ተግባሩ በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታዎቹን ለመወጣት ይህ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልፀው ወደፊት የማህበር አባላትና የማዕከሉን ሠራተኞች በማስተባበር ሰፊ ስራ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የብልፅግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ለተሰጣቸው ስጦታ ከፍ ያለ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments