
መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት የሥራ ባህልና ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የፌዴራል የሚኒስቴሮች ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከልን ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ለጎብኝዎቹ የልህቀት ማዕከሉን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና የመንግስትን ለልማቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በልህቀት ማዕከሉ በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላም እርባታ፣ በማድለብ፣ በመኖ ማቀነባበር፣ በአገልግሎት ዘርፍ በንግድ ሥራዎች ተሰማርተው የመልሶ ማቋቋምና የማልማት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮችና ባለሙያዎችም በተመለከቱት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን አንስተው የዚህ ዓይነት ተቋማት በሁሉም ቦታዎች ተቋቁመው ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት ያለባቸው በመሆኑ ተሞክሮው ተቀምሮ መስፋት ቢችል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments