በእንቬስትመንት ሆልድንግስ ስር ያሉ ተቋማት እና...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    1

በእንቬስትመንት ሆልድንግስ ስር ያሉ ተቋማት እና ከገንዘብ ሚንስቴር የተውጣጡ ከ200 በላይ የሆኑ ጎብኝዎች የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም


በእንቬስትመንት ሆልድንግስ ስር ያሉ ተቋማት እና ከገንዘብ ሚንስቴር የተውጣጡ ከ200 በላይ የሆኑ ጎብኝዎች የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከልን ተገኝተው የዶሮ እርባታ፣ የወተት ላም እርባታ፣ ማድለብ እና ሌሎች በማዕከሉ የሚሰሩ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የማዕከሉን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለጎብኝዎቹ ተዘዋውረው ገለፃ አድርገዋል፡፡


የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በማዕከሉ ከ35,000 በላይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች እንዳሉና በአሁሉ ወቅት ምርት መስጠት እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ማዕከሉ በእንስሳት ምርት አቅርቦት ለከተማዋ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ድርሻ እያበረከተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በማዕከሉ እና ካዛንችስ ሴቶች አደባባይ በሚገኘው የማዕከሉ ምርት መሸጫ ሱቆች እንቁላል በ10.00 (አሥር) ብር እንዲሁም ወተት በ75.00 (ሰባ አምስት) ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም ማዕከሉ ይዞት የተነሳው ራዕይ ሰፊና ከከተማዋም አልፎ ለሀገር የሚጠቅም በመሆኑ ማዕከሉን ከመደገፍ አኳያ እኛም እንደየ ተቋማችን ተልዕኮ የበኩላችንን ሚና የምንወጣ ይሆናል ብለዋል፡፡


ማዕከሉ ከሚያመርተው ምርት ጎብኝዎቹ ተጋብዘው እንዲሄዱ መደረጉም የተለየ ስሜት የፈጠረባቸው መሆኑን አንስተው ለተቋሙና ለአጠቃላይ ሰራተኞቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments