በተቋማት የከተማ ግብርና ስራ  በተቀናጀ አግባብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በተቋማት የከተማ ግብርና ስራ  በተቀናጀ አግባብ እያደገ መቷል።

በተቋማት የከተማ ግብርና ስራ  በተቀናጀ አግባብ እያደገ መቷል። 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም 

የ2017 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር"የሌማት ትሩፋት"የ44 ቀን የንቅናቄ ስራ እቅድ አፈፃፀም  ተገመገመ። 

አፈፃፀሙ የተገመገመው  የከተማ ግብርና  ዘርፍ ም/ኮ  አቶ መለስ አንሸቦ፣የአርሶ አደር ማቋቀምናልማት ዘርፍ ም/ኮ  ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እና የኳራንቲን ሰርተፍኬሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮ  ፀጋ ለማ(ዶ/ር)  ባሉበት የሁሉም ክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር  ነው የተገመገመው። 

[  ] በመንግስት እና በግል ተቋማት 2414 ነባሮች የቀጠሉ ሲሆን  አዲስ ተጠቃሚዎችን  ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር   በእፀዋት 37,198  በእንስሳት ( እና በዶሮ ሀብት) ደግሞ 31,542 ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል  ተብሏል።

በተጨማሪ  የተፈጠረ  የስራ እድል  በኢንተርፕራይዝ 77፣1,961፣በቅጥር 424፣በፋሚሊ  ቢዝነስ 2,128እና አርሶ አደር መልሶ በማቋቋም ማህበራት 45(293)ተጠቃሚዎች ወደስራ እንደገቡ በሪፓርቱ  ቀርቧል። 

የንቅናቄ ስራውን  በየሳምንቱ  ከዘርፉ ጋር በየደረጃው መገምገሙ፣የግብአት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ትስስር  መፍጠር እና በተቋማት  የከተማ ግብርና  ስራ  በተቀናጀ አግባብ እያደገ መምጣቱ  በጥንካሬ የታዩ ጎኖች ሲሆኑ ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ  ሪፓርት አለመላኩ ፣የስራ እድል ፈጠራ ሁሉም ወረዳ ላይ እኩል አለመጀመሩና የንቅናቄና ወቅታዊ ስራዎችን  አቀናጅቶ አለመምራት በጉድለት የታዩ  ናቸው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments