ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም


ከኢኮኖሚ ሴክተሮች የተውጣጡ ከ270 በላይ የሆኑ ጎብኝዎች የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ መንግስት እየሰራቸው ካሉ ሰው ተኮር ሥራዎች መካከል አንዱ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል መሆኑን ገልፀዋል፡፡


አክለውም በማህከሉ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላም እርባታ፣ በማድለብ፣ በመኖ ማቀነባበር፣ በአገልግሎት ዘርፍ በንግድ ከ500 በላይ የሚሆኑ ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው በማዕከሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡


የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በማዕከሉ ከ35,000 በላይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች እንዳሉና በአሁሉ ወቅት ምርት መስጠት እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ማዕከሉ በእንስሳት ምርት አቅርቦት ለከተማዋ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ድርሻ እና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም በተመለከቱት ልማት መደሰታቸውን እና ተሞክሮውን ለማስፋት የራሳቸውን አበርክቶ የሚወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለተደረገላቸውም አቀባበልና መስተንግዶ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments