ቅንጅታዊ  አሰራር  ወደተሻለ ደረጃ  ያሸጋግራል

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ቅንጅታዊ  አሰራር  ወደተሻለ ደረጃ  ያሸጋግራል

ቅንጅታዊ  አሰራር  ወደተሻለ ደረጃ  ያሸጋግራል

 አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን  ከቅንጅታዊ ተቋማት  ጋር  የ2017 በጀት  ዓመት  የ9 ወር 
የቅንጅታዊ ስራዎች  እቅድ  አፈፃፀም  ሪፖርት   ተገመገመ፡፡

አካባቢን መሰረት ያደረገ የከተማ ግብርና፣የአርሶ አደሩ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፤ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የግብርና ምርት እና የተሻሻለ ግብዓትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም  የኮሚሽኑ  የትኩረት መስኮች ናቸው፡፡

ከቅንጅታዊ  ተቋማት  ጋር በጋራ በመሆን የአርሶ አደር የይዞታ መጠቀሚያ መብት ፈጠራ ስራዎች እንዲጠናቀቅ ከማድረግ አንፃር ስራው በቅንጅት እንዲመራ ተደርጓል፡፡ ስለሆነም አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ  የማመቻቸት  ስራ መሰራቱ፤769 ንግድ ሱቅ  በኮሚሽን ስም በውል የተረከብን መሆኑ፤ካርታ እንዲሰራ ቅድመ ካርታ እንዲሰራ ለመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮና ለ4 ክ/ከተሞች ለመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት መረጃ ተደራጅቶ እንዲቀርብ መደረጉ፣ለሰርቶ ማሳያ ማዕከል ለተያዘ 2 ፕሮጀክት በወተት ከብት እርባታ የተቀናጀ ዓሳ እና ዶሮ ዲዛይን ሥራ በየካ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ጋር በመሰራት ላይ መሆኑ፤በማህበር የተደራጁ 1,965 አርሶ አደሮችን በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በማስገባት እንዲሰለጥኑ መደረጉ፤16,216  /95%/ ዜጎች በከተማ ግብርና ስራ ዘርፎች የስራ ዕድል መፍጠሩ፤የአርሶ አደርና መልሶ ማቋቋሚያ  ሲስተም በማልማትና በማጠናቀቅ  ወደ ስራ መገባት መቻሉ ከቅንጅትታዊ ተቋማት ጋር ተሰሩ ስራዎች  እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡

ለ221,114 አባወራዎች/እማወራዎች በስርዓተ ምግብ ና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቤት ለቤት ክትትሎች  መደረጋቸው፤የከተማ ግብርና ምርት በሸ/ህ/ስ/ማህበራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ማስተሳሰር መቻሉ፤የውሃ መሰረተ ልማት አገልግሎት ጠያቂ አርሶ አደሮች መረጃ በማጣራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ፤የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አገልግሎት ጠያቂ አርሶ አደሮች መረጃ በማጣራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ  ማድረግ መቻሉ፤በከተማ ግብርና የሚመረቱ የጓሮ አትክልቶችና የእንስሳት ተዋፅኦች ባልተበከለ አከባቢ መልማታቸውን ማረጋገጥ  መቻሉ፤የመስራት አቅምና ፍላጎት እና የመስሪያ ቦታ ያላቸዉን አረጋዊያንን በከተማ ግብርና ሥራዎች እንዲሰማሩ  ማድረግ  መቻሉ፣የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በመልሶ ማቋቋም  የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ  ለ32 ማህበራት 156 ተጠቃሚዎች ብር 41,740,000.00 የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ  መደረጉ፤የ122 ማህበራት /652 አባለት/  የንግድ ስራ ዕቅድ ከስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በጋራ ገምግሞ የማጸደቅ ስራ  መሰራቱ   በትስስራችን መሰረት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ናቸው ተብሏል፡፡

በዕቅድ ተይዘው ያልተከናወኑ ተግባራትን በመለየት በልዩ ትኩረት መፈጸም፤በመረጃ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ መረጃ ተናባቢነትን ማረጋገጥ፤የጋራና የተናጥል ክትትል እና ድጋፍ እና ግምገማ ሥራዎች ማጠናከር  የመሳሰሉት በቅንጅት ሥራዎቻችን ላይ  ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments