
አምራች እጆች የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣሉ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
ከማህበራዊ ሴክተሮችና ምክርቤት የተውጣጡ ከ250 በላይ የሆኑ ጎብኝዎች የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ትናንት አምራች የነበሩ እና ከራሳቸው አልፈው ለሌላ አጉራሽ የነበሩ እጆች ከይዞታቸው በመፈናቀላቸው በጎዳና እና የእምነት ተቋማት ተጠግተው የነበሩ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ስራ ተሰርቷል፡፡
ከተሰሩ ብዙ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መካከል በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ ከ500 በላይ አርሶ አደሮችን በማህበራት በማደራጀት በማድለብ፣በወተት፣ በዶሮና እንቁላል ዘርፍ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ለከተማዋ ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና የዋጋ ንረትን ከመቆጣጠር አንጻር ከፍተኛ ሚና እየተጫዎቱ ይገኛሉ፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም ማዕከሉ ለተሞክሮ መውሰጃ ትልቅ ምሳሌ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments