የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው፡፡

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም


በህገወጥ እንሰሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ላይ    ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ያሉ ተግባራት በተሻለ ቅንጅትና መግባባት  ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የትንሳኤ  በዓልን ምክንያት በማድረግ ህጋዊ ምርመራን ተከትለው በቄራዎች የታረዱ 15679 ከብቶች እንደሚደርሱ  የሰርተፍኬሽን ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር ዶ/ር አስናቀ  አወቀ  ገልጸዋል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ  የእንሰሳት እርድና ሥጋ ዝውውር  ለህብረተሰባችን  ጤንነቱ ያልተጠበቀ ምርት እንዳይደርስ ከሚመለከታቸው  ተቋማቶች ጋር  በቅንጅት  ክትትልና ቁጥጥር  ተደርጓል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ጥራት ያለው ስጋ ከመቅረቡም በተጨማሪ  ጥራቱን የጠበቀ ቆዳና ሌጦ   እንዲገኝ  ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል ፡፡     

ለከተማዋ የሚቀርቡ የሥጋ ምርት ግብዓትና አገልግሎት ጥራት፣ ጤንነት እና ኃይጅን  ቁጥጥር አሰራርን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን በመሆኑ በእንሰሳት ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰሩ ድርጅቶችን ላይ እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡና የብቃት ማረጋገጫ እንዲያወጡ  ተደርጓል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments