
ለሰው ተኮር ተግባር ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት
ለሰው ተኮር ተግባር ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ግብርና ጽ/ቤት የ2ኛ ዙር 4ኛ ወር የሌማት ትሩፋት ንቅናቄን ምክንያት በማድረግ በስሩ ላሉ ለሁሉም ወረዳዎች የዶሮ ጫጩት12,600 ፣የዶሮ ኬጅ 1960፣የንብ ቀፎ 400 እና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችን 120 ኪ.ግ እና 370 ኩንታል መኖ በአጠቃላይ አሰራጭቷል፡፡
የሌማት ትሩፋት መርሀግብር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጭነት እና በአመራሩ ርብርብ ወደስራ የተገባ ሲሆን ዋና አላማው የገበያ ዋጋ ማረጋጋትና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው ፡፡(የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ)
ትናንት ጥቅም ሳይሰጡ ታጥረው የነበሩ ቦታዎች ዛሬ ግን በብዙ ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮበታል ብለው ኮሚሽነሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 8 በሚገኘውን አዲስ የንብ ክላስተር የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ፣የአቃቂ ቃሊቲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮ አቶ መለስ አሸቦ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ኡርጎ እና የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ሀዋዝ አስፋው በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ሰው ተኮር ተግባር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ አመራሮች እና ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ አህመድ ኡርጎ ናቸው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments