ኦዲት ዓላማው መማማር ነው፡፡

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ኦዲት ዓላማው መማማር ነው፡፡

ኦዲት ዓላማው መማማር ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር የኮሚሽኑን የ2016 በጀት ዓመት ፋይናንሻል ኦዲቲ ሪፖርት መነሻ በማድረግ የመውጫ ኮንፍረንስ አድርጓል፡፡

በወ/ሮ አንድነት ብዙሰው (የፋይናንሻል ህጋዊነት ኦዲት ም/ዋ/ኦዲተር) የተመራው ቡድን የኦዲት ግኝት ሪፖርቱን በዝርዝር አቅርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ወ/ሮ አንድነት ብዙሰው ኦዲት ዓላማው መማማር በመሆኑ ኮሚሽኑ ግዙፍ የሆነ በጀት እንደማንቀሳቀሱ የተገኙ ግኝቶች ብዙ ባይባሉም ወስዶ ማስተካከልና ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በሪፖርቱ መሰረት የሚመለከታቸው የኮሚሽኑ ሥራክፍሎችም የተገኙ ግኝቶች ላይ ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መስተካከል ያለባቸውንም ለማስተካከል የሚመለከታቸውን የወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮሚሽኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ የኦዲት ቡድኑ ያቀረበው ሪፖርት አስተማሪ እንደነበረና መስተካከል የሚገባቸው እንደሚስተካከሉ፤ ቀሪወቹ ደግሞ ለቀጣይም ትምህርት የሚወሰድባቸው ተናግረዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የቀረበው ሪፖርት ገላጭ መሆኑን ጠቅሰው መስተካከል የሚገባቸውን የሚመለከታቸው ሥራ ክፍሎች ፈጥነው አስተካክለው ምላሽ እንዲሰጡ፤ ለቀጣይ ትምህርት በሚሆኑት ጉዳዮች ላይ ደግሞ ተቋሙ የዕቅዱ አካል አድርጎ ሊሰራባቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments