
ዕቅድ የቀደመውን ሥራ አፈፃፀም መነሻ አድርጎ የቀጣይ በጀት ዓመት ኢላማ ቆጥሮ የሚቀመጥበት የሥራ መመሪያ ነው።
ዕቅድ የቀደመውን ሥራ አፈፃፀም መነሻ አድርጎ የቀጣይ በጀት ዓመት ኢላማ ቆጥሮ የሚቀመጥበት የሥራ መመሪያ ነው።
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የ2018 በጀት ዓመት ፊዚካልና የበጀት ዕቅድ ዝግጅትን በተመለከተ የኮሚሽኑ ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
የኮሚሽኑ የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ቢሻው ለውይይት የሚሆን የመነሻ ሰነድ አቅርበዋል።
አቶ በላይነህ የዕቅድ ዝግጅቱ የስትራቴጅክ ፕላኑን፣ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም፣ ሀገራዊና ከተማዊ የሆኑ ተቋማችንን የሚመለከቱ ጉዳዮችን መነሻ ያደረገ መሆን ያለበት መሆኑን ገልፀዋል።
የዕቅድ ዝግጅቱ የቀረበውን ቢጋር መነሻ ያደረገ ተተንትኖ፣ ክብደት ኖሮት መዘጋጀት ይገባዋል ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየትና ጥያቄዎች አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ዕቅድ ከበጀት ጋር ተናባቢ ሆኖ መታቀድ እንደሚገባው እና የሥራ መመሪሪያ ሊሆን በሚችል አግባብ ተጠያቂነትን አመላካች ሆኖ መዘጋጀት እንደሚገባው የጋራ ተደርጓል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments