በተመጣጣኝ ዋጋ የእንቁላል ምርትን ለገበያ በማቅ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

በተመጣጣኝ ዋጋ የእንቁላል ምርትን ለገበያ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት እየተሰራ ይገኛል።

በተመጣጣኝ ዋጋ የእንቁላል ምርትን ለገበያ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት እየተሰራ ይገኛል።


አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም


የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል እየተመረተ ያለው ጥራት ያለው የወተት፣ የእንቁላል እና የደለቡ የዳልጋ ከብት ምርት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር የገቡት የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች  በቀን ከ9,000 በላይ እንቁላል  እየጣሉ መሆኑን ማዕከሉ ገልጿል።

በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዙር የገቡ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ምርት  የማሳየት ቁመና ላይ በመሆናቸው ማዕከሉ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ገበያ ላይ በማቅረብ የበኩሉን ኢኮኖሚያዊ ሚና የሚጫወት መሆኑን የተቋሙ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ገልፀዋል።

ይህ ደግሞ ማዕከሉ የሚያመርተውን የእንስሳት ምርት ውጤት በየጊዜው እድገት እያሳየ የሚሄድ በመሆኑ  በምርት አቅርቦት ላይ የራሱን ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚጫወት ይሆናል፡፡

ከምርት አቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በስርጭት ሂደቱ እና በዋጋው ተመጣጣኝነት ደስተኛ  መሆናቸውን ግዥ ሲፈፅሙ ያገኘናቸው ሸማቾች አስተያየት ሰጥተዋል።

በማዕከሉ የገበያ እና ሥራ አመራር ቡድን መሪ ወ/ሮ ሣራ ንጉሴ በበኩላቸው ስርጭቱ በተገቢው መንገድ እንዲቀጥልና ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘርፉ ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በማዕከሉ ያለው የምርት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ግለት የቀጠለ መሆኑን ገልፀው ይህ ምርት የስርጭት አድማሱ ከማዕከሉ መሸጫ ሱቆች በተጨማሪ በአቧሬ የሴቶች አደባባይም በየቀኑ ከ4,000 በላይ የእንቁላል ምርት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።

ኃላፊው ይህ የገበያ ዋጋን ከማረጋጋት አንፃር ቀላል የማይባል ሚና እንዳለው ጨምረው አንስተዋል።

በተያያዘ በማዕከሉ የሚመረተው ምርት ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖረው በቅርብ አሰራር የማዘመንና ጠንካራ ክትትል የማድረግ ሥራ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡

መረጃውን ያደረሰን፦ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የኮሙኒኬሽን ፎካል ፐርሰን ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments