ከተማ ግብርና ግቡ የከተማዋን ነዋሪ የምግብ ዋስ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ከተማ ግብርና ግቡ የከተማዋን ነዋሪ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ነው።

ከተማ ግብርና ግቡ የከተማዋን ነዋሪ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ነው።


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 04 ቀን 2017 ዓ.ም



በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሚሽኑን የሦስተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ በመስክና በቢሮ የአፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።
የተከበሩ አቶ ጋትዎች ዎር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ  የከተማ ግብርና በርካታ ሥራዎች የተሰሩበት ዘርፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 


አክለውም ሥራን ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ በቡድን ተቀናጅቶ ከመስራት አንፃር፣ ቴክኖሎጂን ከመጠቀም አኳያ እና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ የተሻለ ሥራ መኖሩን መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም በመስክ በጥንካሬና በክፍተት የተመለከቱትን ሪፖርት ከቀረበው የኮሚሽኑ ዕቅድ አፈፃፀም ጋር በማናበብ አንስተዋል።


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ቋሚ ኮሚቴው ያነሳቸው ጉዳዮች ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚረዱ መሆኑን አንስተው የከተማ ግብርና አሁን ላይ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ኖሮት ለብዙዎቹ ከለት ፍጆታ አልፎ የሥራ ዕድል በመፍጠር የገቢ ምንጭ ሆኗል ብለዋል፡፡


አክለውም የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት መኖ ከሚያመርቱ ባለሃብቶች ጋር ትስስር ከመፈፀም ባሻገር አርቢዎች በራሳቸው መኖ ማምረት የሚችሉበትን ዕድልም እየፈጠርን እንገኛለን ብለዋል፡፡


የኮሚሽኑ የዘርፍ ኃላፊዎች እና ዳይሬክቶሬቶች በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው ላደረገው ድጋፍና ክትትል ምስጋናቸውን አቅርበው የተነሱ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጋትዎች ዎር ኮሚሽኑ መሬት ላይ በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሰራ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments