ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡


አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም 


በከንቲባ ጽ/ቤት የተጠሪ ተቋማት የመልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ክትትል ዘርፍ የኮሚሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት ሥራዎች አፈጻጸምን ምልከታ አደረገ፡፡

የድጋፍና ክትትትል ቡድኑ የኮሚሽኑን የተግባር ምዕራፍ ሥራዎችን በተደራጀ ቼክሊስት በዝርዘር ተመልክተዋል፡፡

የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ የተደረገው ድጋፍና ክትትል አስተማሪ በመሆኑ በቀጣይ ለሚኖረን መደበኛና የንቅናቄ ሥራዎች አፈፃፀም ትልቅ አቅም ይሆነናል ብለዋል፡፡

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከንቲባ ጽ/ቤት በዚህ መልኩ የተግባር ምዕራፍ ላያ ያለንን የዕቅድ አፈፃፀም ምልከታ ማድረጉ ለቀጣይ ሥራችን የጎደለንን በመሙላት በተሻለ እንድንፈጽም ያግዘናል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ ዳይሬክቶሬቶችም የተደረገው ድጋፍና ክትትል ገንቢ አስተያየት የተገኘበት በመሆኑ የድጋፍና ክትትል ቡድኑን አመስግነዋል፡፡

የድጋፍና ክትትል ቡድኑም በምልከታው የተመለካታቸውን ጥንካሬዎችና ክፍተቶች በማንሳት በቀጣይ መወሰድ ያለባቸውን እርምቶች አመላክቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments