
ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ለጤናማ ሕይወት!
ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ለጤናማ ሕይወት!
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
ግብርና እና ሥርዓተ-ምግብ የጠበቀ ግንኝነት እና ተመጋጋቢ የሆነ ጥምረት አላቸው፡፡ የግርና ምርትና ምርታማነትን መጨመር የሥርዓተ-ምግብ ትግበራ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ሀገራት ከተባበሩት መንግስታት የሥርዓተ-ምግብ ፕሮግራም እሳቤ ጋር የተቀናጀና የተጣጣመ የሥርዓተ-ምግብ ፕሮግራም በመቅረጽ ተግባራዊ እያደረጉ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በዘርፉ ላይ ያሉትን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር የምግብና የሥርዓተ-ምግብ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅታ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች፡፡
የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ሥራ በጣም ሰፊ እና በቅንጅት የሚሰራ በተለይም እናቶችና ህፃናት ላይ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የሥርዓተ-ምግብ አማካሪ የሆኑት ዮሴፍ ኃይሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከምግብና ሥርዓተ-ምግብ ችግሮች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳቶችን ለመቀነስ የግብርናው ዘርፍ የተጣለበትን የማምረት ግብ ማሳካት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
የአርሶ አደሮች ኑሮ ዘዴ ማሻሻያ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ገዳምነሺ ፈንቴ ሥርዓተ-ምግብን ስናነሳ የምርት ደህንነት አብሮ የሚነሳ በመሆኑ የተመረተው ምርት ጥራቱና ደህንነት ተጠብቆ ለምግብነት መዋል አለበት ብለዋል፡፡
አክለውም የምግብና የሥርዓተ-ምግብ ትግበራን ለማሻሻል የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ተግባራዊ መደረጉ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ከምግብና ከሥርዓተ-ምግብ አቅርቦት ጋር በተያያዘ እየተሰጠ ያለው ስልጠና እጅግ በጣም ጥሩ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው እና አፈፃፀሙንም ወደታች ወርዶ ኮሚሽኑ መገምገም እንዳለበት አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments