የግብርና ምርት እና ግብዓቶች ጤንነት ደህንነትና...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

የግብርና ምርት እና ግብዓቶች ጤንነት ደህንነትና ጥራት በማስጠበቅ ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል፡፡

የግብርና ምርት እና ግብዓቶች ጤንነት ደህንነትና ጥራት በማስጠበቅ ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል፡፡


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም


የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ በዘርፉ ላሉ ባለሙያዎች በደንብ ቁጥር 96/2010 እና የሥጋ ማጓጓዣ ተሸከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለመስጠት የቀረበ አሰራር ላይ ስልጠና ሰቷል፡፡   

የዘርፉ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የግብርና ምርትና ግብዓት ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ሥራዎችን በአዋጅ፣ በደንብ፣ በመመሪያንና በአሰራር ደህንነትና ጥራት ተጠብቆ በሰው ልጅ ጤናና በአካባቢ ብክለት ጉዳት እንዳይከሰት በመከላከል ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ሌላው በመንግስት፣ በማህበራትና በግል ቄራ ድርጅቶች ያሉ የሥጋ ማጓጓዧ ተሸከርካሪዎች ስታንዳርድ አሟልተው ወደ ሥራ መግባት ስለሚጠበቅባቸው ይህንንም በተግባር መሬት ላይ ለማውረድ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን ኃላፊው አንስተዋል፡፡

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አስናቀ አወቀ በበኩላቸው ህግና አሰራርን በማስከበር እና ህገ-ወጥነትን በመከላከል ህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የባለሙያውን እና የተጠቃሚውን አቅም መገንባት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ላይ ተሳታፊ የነበሩት የዘርፉ ባለሙያዎችም የተሰጠው ስልጠና የባለሙያውን አቅም የሚገነባ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ባለሙያዎቹ አያይዘውም ተገልጋዮች ለአገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የተሻለ ግንዛቤ ኖሯቸው እንዲሰሩ ከህግና አሰራር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መመቻቸት ያለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments