ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት ባህል መሆን አለበት፡...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት ባህል መሆን አለበት፡፡

ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት ባህል መሆን አለበት፡፡


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም


ከ150 በላይ የሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የሥራ እንቅስቃሴን ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ፣ ም/ኮሚሽነሮች፣ የማዕከሉ ኃላፊ እና የማዕከሉ ባለሙያዎች ለጎብኝዎቹ አቀባበልና መስተንግዶ አድርገዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የንግዱ ማህበረሰብ ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆን ባደረገው የልማት ተሳትፎ መንግስት ይህንን የመሳሰሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እየሰራ ለመሆኑ ማዕከላችን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ 

አያይዘውም በልህቀት ማዕከሉ በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላም እርባታ፣ በማድለብ፣ በመኖ ማቀነባበር፣ በአገልግሎት ዘርፍ በንግድ ሥራዎች ተሰማርተው የመልሶ ማቋቋምና የማልማት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩ የንግዱ ማህበረሰብም በተመለከቱት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን አንስተው የዚህ ዓይነት ተቋማት በሁሉም ቦታዎች ተቋቁመው ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት ያለባቸው በመሆኑ ተሞክሮው ተቀምሮ መስፋት ይገባዋል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments