
መምህራንና የትምህርት አመራሮች የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልን ጎበኙ።
መምህራንና የትምህርት አመራሮች የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልን ጎበኙ።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሚካሄደው ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ዉይይት ላይ የሚሳተፉ የመዲናችን መምህራንና የትምህርት አመራሮች በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ሥራዎችን ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የቡድኑ አስተባባሪና የጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ትውልድን የሚቀርፁ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ማየታቸው ለሌሎች የልማት ሥራዎቹን ለማሳወቅ እና ለልማት ስራው ውጤታማነት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የትምህርት ማህበረሰቡ በየትምህርት ቤቱ የከተማ ግብርና ሥራዎችን በሥፋት ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ለሥራዎቹ አዲስ ባይሆንም በልህቀት ማዕከል ደረጃ እንደዚህ ዓይነት ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን መጎብኘቱ ያለበትን ተቋም የግብርና ምርት ማዕከል ከማድረግ ባለፈ ምርምሮችን በማድረግ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች ተፈጥረው ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ የበኩሉን ያደርጋል ብለዋል፡፡
የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ የትምህርት ማህበረሰቡ በጉብኝቱ ደስተኛ መሆኑን አንስተው መምህራን እና የትምህርት አመራሩ ማዕከሉን እንደጎበኘ ሁሉ ተማሪዎችም ወደ ማዕከሉ መጥተው ቢጎበኙ ይዘውት የሚመለሱት ልምድና ተሞክሮ ለሌሎች በቀላሉ መስፋት ይችላል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments