
የሌማት ትሩፋት እና የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ ከቁጥር ባለፈ ዜጎች ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል ተባለ፡፡
የሌማት ትሩፋት እና የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ ከቁጥር ባለፈ ዜጎች ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል ተባለ፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እና የሥራና ክህሎት ቢሮ በጋራ በቀን 18/2017 ዓ.ም የ75 ቀናት የሌማት ትሩፉት የንቅናቄ ስራዎች እና የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።
በግምገማ መድረኩ በዘጠና ቀናት የንቅናቄ ዕቅዱ በ35ኛው ቀን የግምገማ መድረክ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀምን ጨምሮ በ75 ቀናቱ የሌማት ትሩፉት ስራዎችና በስራ ዕድል ፈጠራ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ቀርቧል።
ባለፉት 75 ቀናት የሌማት ትሩፉት ንቅናቄ ስራና በስራ ዕድል ፈጠራ የተከናወኑ ተግባራት በበጀት ዓመቱ ለመፍጠር ከታቀደው 300ሺ የስራ ዕድል ፈጠራ በ10 ወራት ከ15 ቀናት ውስጥ ብቻ 324ሺ282 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉ ተገልጿል።
በሌማት ትሩፋት 2ኛ ዙር ንቅናቄ መርሃ-ግብር አምስት ግቦች ተጥለው ወደ ተግባር መገባቱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለ9ሺ528 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተመላክቷል።
በንቅናቄ በተሰራው ስራ የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ጥረት መደረጉንና የከተማ ግብርና ስራ ባህል እየሆነ መጥቷል ተብሏል ነገር ግን ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ ዋጋ ከማረጋጋት አንፃር አሁንም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ሥራ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ የቤተሰብ ፍጆታን ለማሟላት ያገዘ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ አበርክቶ ያለው በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያትም ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments