ምርትና ምርታማነት ሁሉን አቀፍ አሳታፊ አሰራር...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ምርትና ምርታማነት ሁሉን አቀፍ አሳታፊ አሰራር በመዘርጋት የሚመጣ ውጤት ነው፡፡

ምርትና ምርታማነት ሁሉን አቀፍ አሳታፊ አሰራር በመዘርጋት የሚመጣ ውጤት ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም


የተቋም አመራርና ሰራተኞች፣ ቅንጅታዊ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት፣ ሲቪክ ማህበራት እና ሌሎችም ያገባኛል ባይ ግለሰቦች ንቁ ተሳትፎ አንድ ተቋም ላስቀመጠው ራዕይ መሳካት ሚናቸው የማይተካ ነው፡፡

ቻይና ኤድ (China Aid) የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ውስጥ የከተማ ግብርና ሥራን ማገዝ የሚያስችሉ በርካታ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

በማዕከሉ ውስጥ እየሰራ ያለው የግብርና ሥራ ከሰርቶ ማሳያነት ባለፈ ለዘር ብዜት እና ለምርትና ምርታማነት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትንም በስፋት ማሳተፍ እንደሚገባ የኮሚሽኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ ገልፀዋል፡፡

የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብደታ ደሜ ድርጅቱ የስልጠና አዳራሽ እድሳት፣ የእንጉዳይ ዘር ብዜት ላብራቶሪ እድሳትና ግብዓት ማሟላት፣ 32 ሜ. × 8 ሜ. የሆነ የግሪን ሃውስ ዝግጅት፣ 160 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የዶሮ ቤት ግንባታ፣ ከ800 ካሬ ሜትር በላይ የሚሸፍን ሰባት ዓይነት ዝርያ ያለው የበቆሎ ዘር ሰርቶ ማሳያ፣ ሰባት ዓይነት የእንጉዳይ ዘር እና የጓሮ አትክልት ዘር አቅርቦት፣ የትራክተር ጥገና፣ ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ እና ግቢውን በማስዋብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የቻይና የግብርናው ዘርፍ አመራሮችም በአካል ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በስፋት ለማገዝ ቃል መግባታቸውን አቶ አብደታ ደሜ ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ ለልምድና ተሞክሮ እንዲሁም ለተግባር ተኮር ሥልጠና ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments