
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ለመቆጣጠር የተቋቋመው የጋራ ግብረ-ኃይል በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ለመቆጣጠር የተቋቋመው የጋራ ግብረ-ኃይል በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
በመዲናችን አዲስ አበባ አሁን ያለውን ወቅታዊ የልማት እና የዕድገት ደረጃ የማይመጥን ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ይስተዋላል፡፡
ህገ-ወጥ እንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ለመቆጣጠር ከአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ንግድ ቢሮ፣ አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትና ሌሎች ተቋማትን ያካተተ የጋራ ግብረ-ኃይል ተቋቁመዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመቆጣጠርና ለመከላከል እንዲቻል እንዲሁም ባለቤት ለመፍጠር እና ለችግሩ ቋሚ የሆነ መፍትሄ ለመስጠት ግብረ-ኃይሉ የማስፈፀሚያ ዕቅድ አዘጋጅቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ አድርጓል፡፡
ውይይቱን የመሩት የግብረ-ሃይሉ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ስር ሰዶ የሚገኘውን ህገ-ወጥ እንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር በዘላቂነት ለመቆጣጠርና ለመከላከል በቅንጅት ካልሆነ በስተቅር በተናጠል ውጤት ማምጣት ፈፅሞ የሚቻል ባለመሆኑ ተቋማት በቅንጅት መሰራት አለባቸው ብለዋል፡፡
አያይዘውም ህገ-ወጥ እንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ለጤና ችግር፤ ለግብር ስወራ፤ ለከተማ ፅዳት መጓደል፤ ለሰላምና ፀጥታ መደፍረስ እና ፍትሃዊ ላልሆነ የንግድ ሥርዓት መስፋፋትና መሰል ችግሮች የሚያመጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአብይ ኮሚቴው አባላትም በበኩላቸው ስራውን በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ በእቅዱ ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ቀጣይ የስራ ስምሪት መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments