የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ የላም ዝርያ መረጣ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ የላም ዝርያ መረጣና ማኔጅመንት ወሳኝነት አለው፡፡

የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ የላም ዝርያ መረጣና ማኔጅመንት ወሳኝነት አለው፡፡


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም


የተሻሻለ የእንስሳት ዝርያዎችን በመምረጥ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና አግባብነት ያለው የማኔጅመንት ሥራ በመስራት የወተት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል ዶ/ር ገዳ ረጋሣ ለእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች እና ለተጠቃሚዎች ስልጠና በሰጡበት ወቅት ገልፀዋል፡፡


እየተካሄደ ባለው ውጤታማ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ ሥራ አርቢዎች በመንግስት እና በሌሎች በዘርፉ በተሰማሩ አካላት አማካኝነት የተሻሻለ ዝርያ የማዳቀል አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን የእንስሳት እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ካሳሁን ብሩ ገልፀዋል፡፡


አርቢዎች ከዝርያ መረጣ ባሻገር ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ ለላሞች የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የሚፈለገውን የወተት ምርት ማግኘት እንደሚቻል በስልጠናው ተገልጿ፡፡


አርቢው የተሻሻሉ የወተት ላም ዝርያን የሚጠቀም ከሆነ እና ተገቢውን እንክብካቤ ካደረገ የከተማዋን ነዋሪ የወተት ፍላጎት ማሟላት ይቻላል፤ አርቢውም ኢኮኖሚካሊ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡
ስልጠናው በዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) አጋርነት እየተሰጠ ያለ ሲሆን ድርጅቱ በተመረጡ ወረዳዎች ላይ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ስልጠናዎችና ሌሎች ድጋፎችንም እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡


እየተካሄደ የሚገኘው የወተት ላም ዝርያ የማዳቀልና የማሻሻል ሥራም ገበያ ላይ እየጨመረ የመጣውን የወተት ላም ፍላጎትና የዋጋ ንረት በማረጋጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
ሌላው የተሻሻሉ ጊደሮችን በመግዛት፣ ጥራት ያለው መኖ በማቅረብ፣ የእንስሳት አያያዝ አቅም በማሻሻል፣ እንስሳቱ ክትባትና ሕክምና በወቅቱ እንዲያገኙ በማድረግ የሚጠበቀውን ምርት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments