
ዜና ትንታኔ
ዜና ትንታኔ
ማዕከሉ ከምርት አቅርቦት ባሻገር ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ሆኗል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት እና ምርታማነት ላይ ከሚሰራው ሰፊ ሥራ ባሻገር የልምድና ተሞክሮ መቅሰሚያ የእንስሳት እርባታ ማዕከል እየሆነ ነው፡፡
በርካታ ጎብኝዎች ከመዲናችን አዲስ አበባ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል፣ ከተለያዩ ተቋማት፣ ከክልሎች እና ከሀገር ውጭም እየመጡ ልምድና ተሞክሮ እየወሰዱ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው የሚያዝያና የግንቦት ወር ብቻ በርካታ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሃይማኖት ተቋማት አባቶችና ምዕመናን፣ የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮችና ደጋፊዎች፣ ወዘተ በማዕከሉ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በማዕከሉ ውስጥ በተመለከቱት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ገቢ አስተያየት ሰጥተዋል፤ አንዳንዱቹም በአጋርነት ለመስራት ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
ማዕከሉም ያገኘውን አስተያየት የዕቅዱ አካል አድርጎ ሰፊ የሆነ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ከተለያ የማህበረሰብ ክፍል የተውጣጡ ጎብኝዎች በተለያየ ጊዜ ወደ ማዕከሉ መጥተው ጉብኝት ማካሄዳቸው የተጀመረውን የከተማ ግብርና የማስፋፋትና የማዘመን ስትራቴጂ በቀላሉ ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እናዳለው ገልፀዋል፡፡
አክለውም ከተማችን ላይ የሚታየውን የግብርና ምርት አቅርቦት የበለጠ በማሳደግ የዋጋ ማረጋጋት ሚናውን ከፍ ለማድረግ በከተማ ግብርና ሥራዎች እና በሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የተጀመረውን ሰፊ ሰው ተኮር ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አጋዥ እንዲሆን የተደረጉት ጉብኝቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ጎብኝዎች በተለያየ ጊዜ ከተለያ ዘርፍ ወደ ማዕከሉ መጥተው መጎብኘታቸው ለጎብኝዎቹ ብቻ ሳይሆን ለእኛም በርካታ ትምህርቶችን ያገኘንበት በመሆኑ የተሰጠንን አስተያየት የዕቅዳችን አካል አድርገን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል በመምጣት ጉብኝት ያደረጉ አካላትም በተመለከቱት መልካም ስራ የተደሰቱ መሆኑን ገልፀው የበለጠ መስፋትና በሌሎች ቦታዎችም ላይ የዚህ ዓይነት ማዕከላት ተገንብተው ወደ ስራ መግባት ያለባቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments