
የእንስሳት ደህንነት ጥበቃ የሚፈለገውን ምርት ለማግኘት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡
የእንስሳት ደህንነት ጥበቃ የሚፈለገውን ምርት ለማግኘት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የእንስሳት ደህንነት የእንስሳቱ ሁለንተናዊ ጤንነት ጥበቃ ማለት ሲሆን በሁሉም የእንስሳት እርባታ በመኖሪያ ቤታቸው፣ በአመጋገባቸው፣ በመጓጓዣቸው እና በእንስሳት ክትባትና ህክምና የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ተግባር ነው፡፡
የእንስሳት ደህንነት ጥበቃ አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች እንስሳት በአክብሮት እና በርህራሄ መያዝ ስላላባቸው፣ በእንክብካቤ የሚያዙ እንስሳት ጤናማ እና ምርታማ የመሆን እድላቸው ሰፊ ስለሆነ፣ እንስሳት ክትባቶች እና ህክምና በወቅቱ ማግኘት ስላለባቸው ነው፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በማዕከሉ ለሚገኙ ሁሉም ክላስተሮች (የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ፣ የወተት ከብት እርባታ እና የዳልጋ ከብት ማድለብ) በሽታ ለመከላከል የሚሰጡ ክትባቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአግባቡ ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ገልፀዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ ተግባር ከቅድመ በሽታ መከላከል ባሻገር የእንስሳቱን ምርትና ምርታማነትም ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ሌሎች የእርባታ ቦታዎችም ላይ ለእንስሳቱ የሚደረገው የደህንነት ጥበቃ ሥራ በዕቅድ ሊመራ የሚገባው መሆኑን ማሳያ ተግባር ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments