
ከተማ ግብርና ለከተማዋ ዘርፈ ብዙ የሆነ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡ (ተወያይዎች)
ከተማ ግብርና ለከተማዋ ዘርፈ ብዙ የሆነ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡ (ተወያይዎች)
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
ከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ማስግኛ፣ ለሥራ ዕድልና ለዘላቂ አካባቢ ጥበቃ የሚኖረውን አስተዋጽኦ በሚገባ መጠቀም እንዲቻል ድህነትን ለመቀነስና በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን ማህበረሰብ የአመጋገብ ሁኔታ ለማሻሻል ያመች ዘንድ የከተማ ግብርናን አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ ተግባር ነው፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በቦሌ፣ ለሚ ኩራ እና የካ ክፍለ ከተሞች ላይ ከሚገኙ አርቢዎች ጋር የእርባታውን ዘርፍ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ከተማ ግብርና በዘርፉ የተሰማሩ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመጨመሩም በላይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ኮሚሽኑ እና ከተማ አስተዳደሩ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚው (አርቢውና አልሚው) አካባቢ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አበክሮ እየሰራ በመሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎች የመፍትሔው አካል በመሆን የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነሮችም መንግስት ዘርፉን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ተጠቃሚዎች በየደረጃው ያሉ ችግሮችን በመፍታትና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከዘርፉ መገኘት ያለበትን ምርት ለማግኘት ተግተው ሥራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በየደረጃው ያለው አመራር በተለይም ኮሚሽኑ፣ ባለሙያዎች እና ከተማ አስተዳደሩ ዘርፉን ለማሳደግ እያደረጉ ያለውን ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከተማ ግብርና በከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ትልቅ ድርሻ እያበረከተ መሆኑን ገልፀው በተለይ በወረዳ ደረጃ በቅርብ ድጋፍ ሊያደርግልን የሚችል የባለሙያ እጥረት ያለ በመሆኑ ቢታሰብበት ሲሉ ክፍተቱን ጠቁመዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የተነሱት ሃሳቦች ገንቢ በመሆናቸው አጠናክረን እንሰራለን፤ ከመኖ ጋር በተያያዘ የነበሩ ችግሮችን በሚገባ ፈተናል፤ የተገኘውን መልጋም አጋጣሚ መጠቀም የአርቢው ድርሻ ነው፤ ሌላው ውይይቱ በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ እዚህ ያልተነሱ ካሉ ሌሎች ቦታዎች ላይ እያየን የጋራ የሆነ መፍትሐየ እየሰጠን እንሄዳለን ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments