የዕቅድ አፈፃፀምን በጋራ እየገመገሙ መሄድ የጋራ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የዕቅድ አፈፃፀምን በጋራ እየገመገሙ መሄድ የጋራ ችግርን ለመፍታት ወሳኝ ተግባር ነው።

የዕቅድ አፈፃፀምን በጋራ እየገመገሙ መሄድ የጋራ ችግርን ለመፍታት ወሳኝ ተግባር ነው።


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከጠቅላላ ካውንስሉ ጋር አካሂዷል።

በውይይቱም የቁልፍ እና የዐበይት ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም እና ከዕቅድ ውጭ ተጨማሪ ተደርገው የተሰሩ ሥራዎች ሪፖርት በየዳይሬክቶሬቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከቁልፍ ተግባር አንፃር የተቋም ግንባታ፣ ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር፣ ከመልካም አስተዳደር አንፃር፣ ከባለድርሻና ቅንጅታዊ አሰራር ጋር በተያያዘ፣ ሚዲያና ኮሙዮኒኬሽን እንዲሁም ዐብይ ተግባራት ላይ በየግቡ የቀረበው ሪፖርት መልካም መሆኑን ገልፀው ነገር ግን በማስረጃ የተደገፈና ተዓማኒነት ያለው ሪፖርት በየዘርፉ መደራጀት ያለበት መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም በክፍተት የተነሱ ጉዳዮች በጊዜ የለኝም መንፈስ በቅንጆት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የዘርፍ ኃላፊዎች የዘርፋቸውን እና እንደተቋም ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር በማንሳት ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን ለይቶ የቀሪ ጊዜ ዕቅድ ላይ በማካተት ልዮ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየትና ጥያቄ በስፋት አንስተው ተወያይተዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የዕቅድ አፈፃፀም በየደረጃው እየተገመገመ መምጣት እንዳለበት፣ ዘርፎች ዘርፋቸውን በበላይነት ስትራቴጂካል ሆነው መምራት ያለባቸው መሆኑን፣ የተሰሩ ሥራዎች በአግባቡ ተለቅመው የሪፖርት አካል መሆን ያለባቸው መሆኑን፣ ዕቅድ የሥራ መመሪያ ተደርጎ መሰራት ያለበት መሆኑን አጽህኖት ሰጥተው አንስተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments