የእንቁላል ዋጋን ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየተሰራ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የእንቁላል ዋጋን ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።

የእንቁላል ዋጋን ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30 ቀን 2017  ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንቁላል ዋጋን ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየሰራ ሲሆን በሥሩ ካለው የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የሚመረተውን የእንቁላል ምርት ከማዕከሉ ባለፈ በካዛንችስ አቧሬ አካባቢና በዛሬው ዕለት ደግሞ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ የመሸጫ ሱቆችን በመክፈት ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል።

በሁሉም የማዕከሉ ምርት መሸጫዎች እንቁላል በተመሳሳይ ዋጋ በብር 10.00 (አሥር ብር) ብቻ እየተሸጠ መሆኑን እና በአብዛኛው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments