
የተደራጀ የሱፐርቪዢን ሥራ የተጠቃሚዎችን ምርታማነት በእጅጉ ያሻሽላል።
የተደራጀ የሱፐርቪዢን ሥራ የተጠቃሚዎችን ምርታማነት በእጅጉ ያሻሽላል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
በአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት፣ በከተማ ግብርና የእጽዋትና እንስሳት ሃብት ልማት፣ በሬጉላቶሪ እና ምርት አቅርቦት ላይ የተደረገ የሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦ በኮሚሽኑ ጠቅላላ ካውንስል ግምገማ ተደርጓል።
በእንስሳት እርባታና እጽዋት ልማት ዘርፍ በስታንዳርድ አለመስራት፣ የመረጃ አያያዝ ክፍተት፣ የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ውስንነት፣ ወዘተ የመሳሰሉት ክፍተቶች በሱፐርቪዢን ቡድኑ የታዮ እጥረቶች መሆኑ ተነስቷል።
ከምርት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የዋጋ ንረት የታየው ከመኖ ዋጋ ጋር በተያያዘ፣ ገበያው ውስጥ ደላላ መኖሩ፣ አምራችና ሸማቹ በሚፈለገው ልክ ቀጥታ እንዲገናኙ የተሸራው ሥራ ውስንነት፣ ... መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከማዕከል እስከ ተጠቃሚ ተናቦ መስራት፣ መረጃ በአግባቡ መያዝና ተደራሽ ማድረግ፣ የሰንበት ገበያዎችን ማጠናከር፣ አምራችና ሸማቹን ቀጥታ ማገናኘት፣ የገበያ ትስስርን በአግባቡ መምራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም በሱፐርቪዢን ቡድኑ የታዮ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ማስቀጠል ክፍተቶችንም ከላይ እከታች ተናቦ ፈጥኖ መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የዘርፍ ኃላፊዎች የመረጃ ክፍተትን፣ ከላይ እስከታች ተናቦ መስራትን፣ ተጠያቂነትን ማስፈንን ... አድምተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
አክለውም አሁን ያለንበት ጊዜ ጠባብ በመሆኑ ክፍተቶችን ለማረም ቀጠሮ መያዝ ስለማያስፈልግ አሁን ዛሬ ጀምረን በጊዜ የለኝም ስሜት መስራት ተገቢ ይሆናል ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በግምገማ የተነሱ ክፍተቶች ተለቅመው በቀሪ ጊዜ ዕቅድ በየዘርፍ፣ በየዳይሬክቶሬቱ እስከ ባለሙያ ወርደው ተጠያቂነትን ማዕከል አድርጎ እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments