በቅንጅት የሚደረግ ድጋፍና ክትትል ሁሉን አቀፍ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በቅንጅት የሚደረግ ድጋፍና ክትትል ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ሚናው የጎላ ነው፡፡

በቅንጅት የሚደረግ ድጋፍና ክትትል ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ሚናው የጎላ ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም


በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የወተት ጥራትና ግብይት ቁጥጥር ለማከናወን የሚያስችል የህግ ማዕከፍ ለማዘጋጀት ከሚመለከታቸው ቅንጅታዊ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደርጓ፡፡


ከቅንጅታዊ ተቋማት ንግድ ቢሮ፣ ህብረት ሥራ ኮሚሽን፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ LDEI እና ግብርና ባለሥልጣን እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት SNV በተገኙበት የህግ ማዕቀፉ አስፈላጊነትና ዝግጅት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡


የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ በተዘጋጀው ቼክሊስት ላይም የጋራ ግንዛቤ፣ ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት መደረጉን ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የሚደረገው የዳሰሳ ጥናት የህግ ማዕቀፉን ለማዘጋጀት እና የወተት ጥራትና ግብይትን በተሳለጠ መንገድ ለመምራት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡
ይህ ከባለድርሻ አካላት እና ቅንጅታዊ ተቋማት የተውጣጣ የቴክኒክ ቡድን የሚያደርገው የዳሰሳ ጥናት የወተት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት እንደ መነሻ ግብዓት የሚወሰድ ይሆናል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments