በግንቦት ወር ብቻ በማዕከሉ ከ370,000 በላይ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

በግንቦት ወር ብቻ በማዕከሉ ከ370,000 በላይ የእንቁላል ምርት ተመርቷል።

በግንቦት ወር ብቻ በማዕከሉ ከ370,000 በላይ የእንቁላል ምርት ተመርቷል።


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም


በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ባለፈው የግንቦት ወር ብቻ ከ370,000 በላይ የእንቁላል ምርት ማምረት መቻሉን በማዕከሉ የእንስሳት እርባታ፣ ተዋፅኦ እና መኖ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም ኃ/ማርያም ገለፁ።


በዚህ በጀት ዓመት በማዕከሉ ከገቡ 35,500 ያክል እንቁላል ጣይ ዶሮዎች በቀን ከ27,000 በላይ እንዲሁም ባለፈው ግንቦት ወር ደግሞ ከ370,000 በላይ ምርት ማግኘት መቻሉ ተገልጿል። ይህ ምርት አሁናዊ ምርት ሲሆን ዘግይተው ምርት የጀመሩ ዶሮዎች ወደ መደበኛ ምርት ሲገቡ ከፍተኛ የሆነ መሻሻል እንደሚያመጣ ይታመናል።


ከእንቁላል ምርት በተጨማሪ በቀን ከ560 ሊትር በላይ የወተት ምርት፣ ባለፉት 11 ወራት ከ179,000 ሊትር በላይ ጥራቱን የጠበቀ ወተት ማምረት መቻሉ ተገልጿል። ሌላው በበጀት ዓመቱ እስከዚህ ወር ከግዥ ጀምሮ በባለሙያ ክትትልና ድጋፍ 349 የዳልጋ ከብቶችን ማድለብ ተችሏል።


ዝርያን ለማሻሻል ፆታን ለይቶ ማስወለድ የሚያስችል (sexed semen) እና መደበኛ ሰው ሰራሽ ማዳቀል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማዕከሉ ያሉ የወተት ከብቶችን ዝርያ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ቡድን መሪው አንስተዋል።


ተቋሙ የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ማዕከል እንደመሆኑ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሚመጡ አካላት የማማከር አገልግሎት እና ተሞክሮ የማካፈል ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።


በቀጣይ በመኖ ማቀነባበር የተደራጁ ሁለት ማህበራት ወደ ማምረት የሚገቡ በመሆኑ የመኖ ዋጋ እና የአቅርቦት ችግር በመፍታት ምርት እና ምርታማነትን ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸውም ቡድን መሪው ገልፀዋል::ምንጭት፡- ልህቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments