
የቀጣይ ዘጠና ቀናት የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ሥራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጵ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ
የቀጣይ ዘጠና ቀናት የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ሥራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጵ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ የመጡ ለውጦችን ይበልጥ አጠናክሮና አስፍቶ ማስቀጠል ያስፈልጋል።
ገንዘብ ይዞ ገበያ የሚሄዱ ሰዎችን በማብዛት ሳይሆን የግብርና ውጤት የሆኑትን ምርቶች ለራስ ፍጆታ ከማሟላት አንስቶ የገበያ ፍላጎትን በመሸፈን ለሸማቹ ህብረተሰብ ጥያቄ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንደሚያስፈልግ የተከበሩ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።
አክለውም እየገጠሙን ላሉ ጊዜያው ፈተናዎች አንዱ ብርቱ መፍትሔ ጠንክሮ መሥራት፣ መትጋትና ውጤት ማምጣት መሆኑን ገልፀዋል።
በለሚ ኩራ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት የክረምት ንቅናቄ ሥራ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በስፋት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከቀደመው ልምድና ተሞክሮ በመማር ዛሬ ያስጀመርነው የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ፕሮግራምን በስትራቴጅ እንዲመራ ይደረጋል ብለዋል።
አክለውም የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ብዙዎችን ከሸማችነት ወደ አምራችነት እያሸጋገረ ያለ ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments