ፕሬስ ሪሊዝ

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ፕሬስ ሪሊዝ

ፕሬስ ሪሊዝ
ከተማ ግብርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም


ከተማ ግብርና ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ማስግኛ፣ ለሥራ ዕድልና ለዘላቂ አካባቢ ጥበቃ የሚኖረውን አስተዋጽኦ በሚገባ መጠቀም እንዲቻል ድህነትን ለመቀነስና በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን ማህበረሰብ የአመጋገብ ሁኔታ ለማሻሻል ያመች ዘንድ የከተማ ግብርናን አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ ተግባር ነው፡፡


ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል በዘርፉ ለተሰማሩ አካላትን በተለይም ለአርሶ አደሮች፣ በእጽዋት እና በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት አቅም መገንባት፣ የግብዓትና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እና መደገፍ የኮሚሽኑ የዕለት ከዕለት ተግባሩ ነው፡፡


ኮሚሽኑ ከእንስሳት መኖ አቅርቦት እና ዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ከተሰሩት ሥራዎችም መካከል ከሙሌ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከኤም. ኤስ. ኤ. ቢዝነስ ግሩፕ ጋር የተደረገው ትስስር በዋናነት የሚነሳ ይሆናል፡፡


ሌላው መኖን ለአርቢዎች በቅርብ ተደራሽ ለማድረግ ከሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት እና ከሙሌ መኖ ማቀነባበሪያ ድርጅት ጋር በተደረገው የሥራ ትስስር ስምምነት መሠረት ክ/ከተሞችና ወረዳዎች ከአቅራቢያቸው በሚገኝ የመኖ ምርት ማከፋፈያ /ሽያጭ/ መጋዘኖች እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡


ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን አቅም መገንባት፣ የግብዓትና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ማሳደግ አግባብነት ያለው በመሆኑ በእንስሳት ሃብት ልማት  ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አርቢዎች ሐሙስ ሰኔ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ቂርቆስ ማኑፋክቸረንግ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ከ1,000 በላይ ለሆኑ ተሳታፊዎች የውይይት መድረክ ያዘጋጀን በመሆኑ የሚመለከታችሁ አካላት በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት በመገኘት ተሳታፊ እና አጋር መሆን የምትችሉ መሆኑን ኮሚሽኑ ይገልፃል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments