የእርባታውን ዘርፍ በማነቃቃት እንስሳትና የእንስ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የእርባታውን ዘርፍ በማነቃቃት እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን ማሳደግ ይቻላል፡፡

የእርባታውን ዘርፍ በማነቃቃት እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን ማሳደግ ይቻላል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 05 ቀን 2017 ዓ.ም


ከተማ ግብርና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥም ባሻገር ለዘላቂ የግብርና ምርትና ግብዓት አቅርቦት የማይተካ ሚና ይጫዎታል፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በልደታ፣ ቂርቆስ፣ አቃቂ እና ን/ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ላይ ከሚገኙ አርቢዎች ጋር የእርባታውን ዘርፍ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡


የከተማ ግብርና ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ በከተማ ግብርና ዘርፉ የተሰማሩ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመጨመሩም በላይ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈረበት ዘርፍ መሆኑን አንስተዋል፡፡


አያይዘውም ኮሚሽኑ በእርባታው ዘርፍ ለተሰማሩት አርቢዎች በተለይም ከመኖ ጋር በተያያዘ የገጠማቸውን ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በየደረጃው ያለው አመራር እና ባለሙያዎች እያደረጉት ያለው ድጋፍና ክትትል መልካም መሆኑን አንስተው ከመኖ ጋር ተያይዞ የተሰራው ሥራ እጅግ በጣም ጥሩና የሚበረታታ በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡


አያይዘውም በሌሎቹም የግብዓት አቅርቦት እና የመስሪያ ቦታ ማመቻቸት ላይ ኮሚሽኑ ሊያግዘን ይገባል ሲሉ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ ከሚመለከታቸው ቅንጅታዊ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት፣ ሲቪክ ማህበራት እና ከራሱ ከተጠቃሚው (አርቢው) ጋር በመሆን አሉ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments