ለ82 ማህበራት የጋራ መኖሪያ ቤት ንግድ ቤቶች...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ለ82 ማህበራት የጋራ መኖሪያ ቤት ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡

ለ82 ማህበራት የጋራ መኖሪያ ቤት ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡ 


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም



በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ እና በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችንና ቤተሰቦቻቸውን ከከተማዋ እድገት ጋር እያለማች ያለች ከተማ፡- አዲስ አበባ፡፡


በልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለተነሱ በ82 ማህበራት ለተደራጁ 400 አርሶ አደሮች እና የአርሶ አደር ልጆች መልሶ ለማቋቋም የመስሪያ ቦታ 82 የጋራ መኖሪያ ቤት ንግድ ሱቆች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡


የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ከተማዋ አርሶ አደሩን ማዕከል አድርጋ ከልማቱ ጋር አብሮ መልማት እንዲችለ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


አክለውም በማህበር ለተደራጁ 400 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች 82 የጋራ መኖሪያ ቤት የንግድ ሱቆች መሰጠቱ እጅግ አበረታች ሲሆን 82ቱን ማህበራት ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ወደ ሥራ ማስገባትና ውጤታማ ማድረግ ግን በየደረጃው ካለው አመራርና ባለሙያ ይጠበቃል ብለዋል፡፡


የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሣ ለየካ 5፣ ለቦሌ 36፣ ለለሚ ኩራ 21፣ ለአቃቂ 7፣ ለን/ላፍቶ 8 እና ለኮልፌ 5 አጠቃላይ ከ6ቱ ማስፋፊያ ክፍለ ከተሞች ለ82 ማህበራት በአባላት ለ400 አርሶ አደሮች 82 የጋራ መኖሪያ ቤት የንግድ ሱቆች የተላለፉላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የጋራ መኖሪያ ቤት የንግድ ሱቁን ቁልፍ የተረከቡት ማህበራትም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም የኮሚሽኑ ድጋፍና ምልከታ እንዳይለያቸው አሳስበዋል፡፡


ሌላዋ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ የሰጡን ወ/ሮ ባህርነሽ አሰፋ ማህበራቱን በቅርበት በመከታተል የተደረገላቸውን ድጋፍ ተጠቅመው ውጤት እንዲያመጡ ይሰራል ብለዋል፡፡


ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል ፈታኝ ቢሆንም አርሶ አደሩ የተደረገለትን ድጋፍ በአግባቡ ተጠቅሞ ውጤታማ መሆን እንዲችል ከላይ እስከታች ያለውን አደረጃጀት በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments