የእንስሳት በሽታ ቅድመ-መከላከል ላይ ትኩረት አ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የእንስሳት በሽታ ቅድመ-መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ምርትና ምርታማነትን ያሳድጋል፡፡

የእንስሳት በሽታ ቅድመ-መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ምርትና ምርታማነትን ያሳድጋል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም


በዘመናዊ እንስሳት እርባታ ዉስጥ ጥብቅ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛዉ የእንስሳት ደህንነት /ባዮሴኩሪቲ/ ነው፡፡


በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል በሁሉም ክላስተሮች የእንስሳት እንክብካቤ እና ጤና አጠባበቅ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን በማዕከሉ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ቡድን መሪ ዶ/ር ኢያሱ ኤጀታ (ተወካይ) ገልፀዋል።


አክለውም በሽታ መከላከል ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ እስከዚህ ወር ድረስ ለወተት ከብቶች 795፣ ለማድለብ 475 እንዲሁም ለዶሮ 140,186 በድምሩ  ከ171,000 በላይ ክትባቶች መስጠት መቻሉን አንስተዋል።


ሌላው በበጀት ዓመቱ እስከዚህ ወር ከ64,000 በላይ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ህክምና መስጠት መቻሉ እና ከ7,000 በላይ ናሙናዎችን በመውሰድ በላብራቶሪ እንዲደገፉ መደረጉ በቡድን መሪው ተነስቷል። 


ለአብነትም በወተት ከብት ክላስተር የአፍተግር /FMD/ በሽታዉን መቆጣጠር መቻሉ እና የጥጆችን ሞት መቀነስ መቻሉ በበጀት ዓመቱ የእንስሳት በሽታ ስርጭትን መከላከል ላይ በተሰራ ሥራ የተገኘ ውጤት ማሳያ ነው፡፡ 


የቡድን መሪው (ተወካዩ) አያይዘውም በቀጣይ በወተት ከብት እርባታ የተጀመረውን የጤና መረጃ ማዕከል /health data center/ በማጠናከር በሌሎች ክላስተሮችም እንዲሰፋ እና ዲጂታል የህክምና አሰጣጥ ሥርዓት በመዘርጋት አገልግሎቱን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የመረጃ ምንጫችን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments