ተቋማት ለጋራ ተልዕኮ በቅንጅት ሲሰሩ የጋራ ስኬ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ተቋማት ለጋራ ተልዕኮ በቅንጅት ሲሰሩ የጋራ ስኬት ያስመዘግባሉ፡፡

ተቋማት ለጋራ ተልዕኮ በቅንጅት ሲሰሩ የጋራ ስኬት ያስመዘግባሉ፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት ተቋማት በቅንጅት ሊሰሯቸው የሚገባ የጋራ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለጋራ ተልዕኮ መሳካት ደግሞ በቅንጅት መስራት ይጠበቃል፡፡

ከአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተውጣጣ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ቁጥጥር ግብረ-ሀይል የስራ አፈፃፀም ግምገማ አድርጓል፡፡

የግብረ-ኃይሉ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተቋማት ለጋራ ተልዕኮ በቅንጅት ሲሰሩ የጋራ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

አክለውም በቅንጅት በግብረ-ኃይል በተደረገ የቁጥጥር ሥራ ህገወጦች ላይ አስተማሪ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቁጥጥር ሥራው በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ላይ ከ10 ቀናት በላይ የተደረገ ሲሆን በ1,145 ተቋማት ላይ ቁጥጥር ተደርጓል፤ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ፈጽመው የታሸጉ ድርጅቶች ብዛት 68 ሲሆን በህገ-ወጥ መንገድ ታርዶ ሲሸጡ የተገኘና የተወረሰ ሥጋ በኪ/ግ 2,446 መሆኑንም ከግብረ-ኃይሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሌላው በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘ ቆዳና ሌጦ 18 ሲሆን እስካሁን ከቅጣት የተሰብሰበ ገንዘብ መጠን በብር 855,000 መሆኑን የግብረ-ኃይሉ ሪፖርት ያመላክታል፡፡
በቅንጅት ተሳታፊ የሆኑት ተቋማት የተሰራው ሥራ መልካም መሆኑን አንስተው በቀጣይ የበለጠ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንደሚገባው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments