
141 ሞዴል ማህበራት ማፍራት ተችሏል፡፡
141 ሞዴል ማህበራት ማፍራት ተችሏል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በአዋጅ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል አንዱ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ ማቋቋምና ማልማት ነው፡፡
በአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ቡድን መሪ አቶ ለገሰ ወርቁ በበጀት ዓመቱ 1,940 አባላት ያሏቸው 388 ማህበራት ማደራጀት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከተደራጁት ማህበራት 32ቱን ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን ከፋይናንስ እና ግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ቀሪዎቹን ወደ ሥራ ማስገባት እንዳልተቻለ አንስተዋል፡፡
ወደ ሥራ የገቡት ማህበራት በከተማ ግብርና ዘርፍ፣ በአገልግሎት እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውንም ቡድን መሪው ገልፀዋል፡፡
አቶ ለገሰ ወርቁ አጠቃላይ እስካሁን ተደራጅተው ወደ ሥራ ለገቡት ማህበራት ኦዲት በማድረግ፣ የቀጥታ ድጋፍ የተደረገላቸውንና ያልተደረገላቸውን ልየታ በማካሄድ፣ ብድር የወሰዱና ያልወሰዱትን በመለየት፣ ቁጠባቸውን አጠናክረው እንዲቆጥቡ በማበረታታት ማህበራቱን በቅርበት መደገፍ ተችሏል ብለዋል፡፡
አክለውም አርሶ አደሩን የማቋቋምና የማልማት ሥራ ከተጀመረ ጀምሮ አጠቃላይ እስከ አሁን ወደ ሥራ ካስገባናቸው ማህበራት መካከል 141 ማህበራት በአፈፃፀማቸው ሞዴል መሆን ችለዋል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments