
የመኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ኮሚሽኑ አሰራር ዘርግቷል።
የመኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ኮሚሽኑ አሰራር ዘርግቷል።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ከተማ ግብርና የከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል።
የከተማ ግብርና ምርት በከተማችን አዲስ አበባ ከ87 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች ላይ ይቀርባል። ይህ ደግሞ የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት አንፃር ሚናው ከፍተኛ ነው።
በተለይ የእንስሳት ምርት አቅርቦት ላይ የሚታዮ ችግሮችን ለመፍታትና ከዘርፉ የሚጠበቀውን ምርት በበቂ ሁኔታ ለማግኘት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።
ኮሚሽኑ በከተማዋ ካሉ አርቢዎች ጋር መድረኮችን በማመቻቸት ችግሮችን ለመፍታት ሰፊ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በዛሬውም ዕለት ከኮልፌ፣ ከአራዳ፣ ከአዲስ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች ከመጡ አርቢዎች ጋር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውይይት አድርጓል።
መድረኩን የመሩት አቶ መለስ አንሼቦ ከመኖ አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ኮሚሽኑ ሰፊ ሥራ እየሰራ በመሆኑ አርቢው ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን ተጠቃሚና አጋዥ መሆን አለበት ብለዋል።
አርቢዎችም በዘርፉ አለ ያሉትን ችግር በዝርዝር አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎ የጋራ የሆነ የቀጣይ አቅጣጫ ተወስዷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments